§ 1በDW.COM ገጽ ላይ የሚታዩ ይዘቶች በአጠቃላይ ለግል ጥቅም ብቻ የታሰቡ ናቸው ። ማንኛውም ተጨማሪ የDW.COM ይዘትን በተለይም ለንግድ ዓላማ መጠቀም ከዶይቸ ቬለ ግልጽ ፍቃድ ውጭ በጥብቅ የተከለከለ ነው ። ይህም ተግባራዊነቱ፦ በሁሉም አይነት ዳግም የማባዛት፣ የማዘጋጅት፣ የማሠራጨት፣ የመተርጎም እና የማይክሮፊሽ (በርካታ ሠነድን በትንሽ ዝርግ ፕላስቲክ ፎቶ የማከማቸት) እንዲሁም ይዘቱን በኤሌክትሮኒካዊ የመረጃ ስርዓቶች ውስጥ ለማጠናቀር በማሰብ የመሰብሰብ ሒደት ላይ ነው ።
§ 2 የእነዚህ ሕግጋት የትኛውም አይነት ጥሰት ባለሥልጣናት ትኩረት እንዲያደርጉበት ይቀርባል ብሎም/አለያይም በፍትሐ ብሔር ሕግ ያስጠይቃል ። DW በድረ ገጹ በኩል በማገናኛ ሊደረስባቸው ለሚችሉ ውጫዊ ገፆች ይዘት ተጠያቂ አይደለም ።
§ 3 ዶይቸ ቬለ በሠራተኞቹ ወይንም በሥራ ተቋራጮቹ ሆን ተብሎ አለያም በከፍተኛ ንዝኅላልነት ካልሆነ በቀር በሥርጭት ስህተቶች፣ መዘግየቶች ወይንም መቆራረጦች፣ በቴክኒክ መሣሪያዎች ብልሽት፣ በቫይረስ ወይንም በማናቸውም መንገድ ለሚደርስ ጉዳት፣ የተሳሳተ ይዘት፣ የሠነድ መጥፋት አለያም መደምሰስ ተጠያቂ አይሆንም ።
§ 4 ለዶይቸ ቬለ የሚቀርቡ መረጃዎች በአጠቃላይ በጥብቅ ምሥጢር ይያዛሉ ። ማናቸውንም የግል መረጃዎች በተመዝጋቢዎች ላልተፈቀደላቸው ዓላማዎች አንጠቀምም ። የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከደረሰን መረጃ የመልቀቅ ግዴታ አለብን።
§ 5 ዶይቸ ቬለ የትኛውንም አይነት ጦማረ-ዜና ሥርጭት በማንኛውም ጊዜ ያለአንዳች ማስጠንቀቂያ የማገድ እና/ወይንም የማቋረጥ መብቱ የተጠበቀ ነው ። የዚህም ተግባራዊነቱ በተለይም በቴክኒካዊ ምክንያቶች ወይንም ሕጋዊ ምክንያቶች ትክክለኛ አፈፃፀም ሊረጋገጥ በማይችልበት ሁኔታ ላይ ነው
§ 6 የትኛውንም አይነት የሚላክልዎ ጦማረ-ዜና በፈለጉት ጊዜ ማቋረጥ ይችላሉ ።
§ 7 ዶይቸ ቬለ አጠቃላይ የአጠቃቀም ሁኔታዎቹን በማንኛውም ጊዜ የመቀየር መብቱ የተጠበቀ ነው ።